Livestock Farming

ቆይታ: 4 ሳምንት


እንስሳት እርባታ

ይህ የትምህርት ክፍል ከብቶችን፣ ፍየሎችን እንዲሁም በጎችን ጨምሮ በከብት እርባታ ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤን ይሰጣል። የእንስሳት ጤናን አጠባበቅ ፣ እርባታን ፣ አመጋገብ ሰልትን ፣ መኖሪያ ቤት አገነባብን ፣ በሽታን መቆጣጠርያ መንገዶችን እንዲሁም ግብይትን በማሳለጥ ዘላቂ እና ትርፋማ የእንስሳት ኢንተርፕራይዞችን አገነባብን ያጠቃልላል።

ዋና ዓላማዎች:
  • በገበያ እና በአየር ሁኔታ ላይ በመመስረት ለእርባታ ሚውሉ የእንስሳት ዝርያዎችን አመራረጥ ዘዴን መገንዘብ።
  • ለእንስሳት ጤና የመኖሪያ ቤት እና የአመጋገብ ስርዓቶችን ማስተካከያ ስልቶችን መረዳት።
  • የመራቢያ እና የበሽታ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ማወቅ።
  • የመዝገብ አያያዝ እና የእርሻ ንፅህናን መጠበቂያ ስልቶችን መረዳት።
  • የእንስሳት እና የእንስሳት ተዋጽኦዎችን በብቃት ለገበያ ማቅረቢያ መንገዶችን ማወቅ።